ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ገንዘብ እንዴት መላክ እችላለሁ?

ከአሜሪካ ውጭ ለሆነ የአሜሪካ ዜጋ ገንዘብ መላክ ከፈለጉ፣ መረጃ ለማግኘት ከግለሰቡ ባንክ፣ የክሬዲት ካርድ ኩባንያ ወይም ከገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች ጋር ማረጋገጥ ይችላሉ።

ከላይ ያሉት አማራጮች የሚሠሩ ካልሆኑ፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ አገር ለሚኖር ችግረኛ የአሜሪካ ዜጋ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ቢሯችን በኩል ወደ አሜሪካ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ፅህፈት ቤት ገንዘቡን በማስተላለፍ ሊያግዝ ይችላል። በውጭ አገር ያሉት የተቸገሩ የአሜሪካ ዜጋ ስለ ብቁነት መስፈርቶች እና ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለመጠየቅ በአቅራቢያ የሚገኘውን የአሜሪካ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ማነጋገር አለባቸው።

ለተጨማሪ አማራጮች እና መረጃ የሚከተለውን ይጎብኙ፦ https://travel.state.gov/content/travel/en/international-travel/while-abroad/sending-money-abroad.html