ልጄ የአሜሪካ ዜግነት ይገባኛል ጥያቄ አለው። ለCRBA ማመልከት አለብኝ?

የውጭ ሀገር ወሊድ የቆንስላ ሪፖርት (CRBA) ከአሜሪካ ዜጋ ወላጅ(ዎች) ሲወለዱ ዜግነት ላገኙ ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ኦፊሴላዊ የዜግነት ማስረጃ ነው። ሁሉም የአሜሪካ ዜጎች ህጋዊ የሆነ የአሜሪካ ፓስፖርት በመጠቀም ወደ አሜሪካ መግባት እና መውጣት ይጠበቅባቸዋል። ስለዚህ፣ ልጅዎ ወደ አሜሪካ የመጀመሪያ ጉዞ ከመጀመራቸው በፊት የልጅዎን የዜግነት ጥያቄ እንዲፈቱ አበክረን እንመክራለን።